Welcome

Anti Essays offers essay examples to help students with their essay writing.

Sign Up

It Is Amharic Essay

  • Submitted by: KShantaya1
  • on April 2, 2014
  • Category: Arts and Music
  • Length: 904 words

Open Document

Below is an essay on "It Is Amharic" from Anti Essays, your source for research papers, essays, and term paper examples.

̋ የት ሄዶ ይለቀስ?   ̋
ጦርነት ሕግ አለው ፡፡የመግደል   የመደምሰስ የማጥፋት እና የማቃጠል ሕግ ነው፡፡ጦርነት ቦታና ጊዜ አይመርጥም ፡፡በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊነሳ ይችላል፡፡ከጦርነት ሁሉ አስከፊው የእርስ በእርስ ጦርነት ሲሆን ነው፡፡በዚህን ጊዜ ሰው ቀዬውን የትውልድ መንደሩን እየለቀቀ ይተማል፡፡እንስሳውም የዱር አውሬውም ሁሉም ግራ ይጋባል፡፡ምድሪቱን የደም አባላ ስለሚውጣት የሠላም አየር አይተነፈስም፡፡በመልካም የአበቦች ሽታ ሳይሆን በአስክሬን ጥንባት ምድሪቱ ትከረፋለች፡፡ዕረፍት እንደ ሠማይ የራቀ ይሆናል፡፡ወዳጅና ጠላት እስኪለይ ድረስ ሰው ሰውን ይፈራል፡፡በጦርነት ጊዜ ከራስ በቀር የሚታመን ወዳጅ በምድር ላይ የለም፡፡
በዚህን ወቅት የጨነቀው እግሩ ወደ መራው ይከንፋል፡፡የሞላ ወንዝ ፣ ዱርና ገደል አያቆሙትም፡፡ሽሽቱ ሕይወቱን ለማትረፍ ብቻ ሳይሆን ነገንም ለመታዘብ ጭምር ስለሆነ ከፊቱ የሚቆምን፣ከመንገዱ የሚያዘናጋውን አይፈልግም፡፡መድረሻውን ሳይሆን ማምለጫውን ነው የሚያስበው፡፡ ፍልሚያው የእርስ በእርስ ስለሆነ የሀገሩ ክልል መደበቂያ ሳይሆን መገደያ ይሆንበታል፡፡ስለዚህም ያለውን ሸክፎ ድንበር አቐርጦ በሰው ሀገር ስደተኛ ይሆንና የሕይወትን ገፈት ‘’ሀ’’ ብሎ መቅመስ ይጀምራል፡፡
ሰው ጓዙን ነቅሎ ሀገር ጥሎ የትናንት ትውስታውን በልቡ ተሸክሞ ወደማያውቀው ሀገር የሚተመው የጦርነትን አሰቃቂ ድርጊት ላለመመልከት ብቻ ሳይሆን ከወላፈኑ አምልጦ በሕይወት ለመትረፍና የትናንት ባለ ታሪክ ሆኖ ደመኞቹን ነገ ለመበቀል ጭምር   ነው፡፡
ዓለም ከሚያውቀው ጦርነት ውጪ ሰው ቀዬውን የሚለቅበት ዋነኛው ምክንያት ደግሞ- ያውቁልኛል ብሎ የሾማቸው ፣ ይጠቅሙኛል ብሎ የመረጣቸው አስተዳዳሪዎቹ ገዢ ሲሆኑበት ፣ ቁም ስቅሉን ሲያሳዩት ፣በረሃብ ጊንጥ ሲገርፉት ፣ በውኃ ጥም ሲያቃጥሉት ፣አትናገር አትይ ብለው የተፈጥሮ ችሮታውን ሲነፍጉት ፣የበላህን እስክናክልህ ድረስ አትከክ ሲሉት ሰው ሀገሩን ብቻ ሳይሆን ሰው መሆኑን ጭምር ይጠላና ይሰደዳል፡፡
ጠግቦ ማደር የለመደ አንጀት በሀገር-ሰላም መራብን አይፈልግም፡፡ረሃብ   አዋርዶ   የተደበቀ ማንነትን የሚገልፅ   ጠላት ነው፡፡ረሃብ አንቱታን አያውቅም፡፡ረሃብ ሰይፍ አይኑረው እንጂ አንጀትን ይቆርጣል፡፡ጦር አይጨብጥ እንጂ ሁለንተንን ይወጋል፡፡ከየትኛውም ዕፅ ይልቅ አዕምሮን ያደንዛል፡፡ረሃብ ትዕግስትን ያስጨርሳል እንጂ ትዕግስትን አያውቅም፡፡አብሮ እየዋለና እያደረ እንደ መልካም ወዳጅ ተጣብቆ ቀናትን ይቆጥራል እንጂ ባለጊዜዎች ውስኪውን እያቃጠላቸው እንደለመዱት ፣ ጮማውን እየቆረጣቸው እንደተወዳጁት እንዲሁ ረሃብ አይለመድም፡፡
ረሃብ እሳት ነው፡፡እንደ ወላፈን ውጪን አይለብልብ እንጂ አንጀትን ያቃጥላል፡፡እሳት በውኃ ይጠፋል፡፡ረሃብን ግን ውኃ አያጠፋውም፡፡ረሃብ ስታለቅስ እየሳቀ ገዝግዞ ይጥልሃል እንጂ ማርኮ ብቻ አይተውህም፡፡
ረሃብ ተፈጥሮ ከሚያመጣው ይልቅ አውቅልሃለው ባዮች ሲያመጡት ቁጭቱ ከረሃቡ ይልቅ ይፋጃል፡፡
ያቺ   ጦር አምጪ ተብላ ምድሯ በጅራፍ ይገረፍ የነበረ ሀገር ፣ ያቺ የእህል ክምራ ግዝፈት በጥይት ይለካባት የነበረ ሀገር ፣ ያቺ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ተብላ የተጠራች ሀገር ፣ ያቺ በብሉልኝ እና በጠጡሉኛ የምትታወቅ ሀገር ፣ ያቺ በስሙኒ ተበልቶ የሚዋልባት ሀገር ዛሬ ያ ሁሉ መታወቂያዋ ጠፍቶ በልጆቿ ዕንባ የምትታጠብ ፣ አዛውንቶቿ የሚያለቅሱባት ፣ ቆንጆዎቿ ስጋቸውን የሚቸረችሩባት፣ እያላት የሌላት ፣ ጡቷን የጠቡ ነካሽ የሆኑባት የወላድ መካን የሆነች ሀገር ….ኧረ የት ሄዶ ይለቀስ፡፡
እንግዲህ በዚህ ሁሉ የግፍ ማዕበል ልብ ቆርጦ አንዴ ከተነሳ መሻቱ ካልሞላለት በዛቻ...

Show More


Citations

MLA Citation

"It Is Amharic". Anti Essays. 14 Dec. 2018

<http://trenmayamx.com/free-essays/It-Is-Amharic-603394.html>

APA Citation

It Is Amharic. Anti Essays. Retrieved December 14, 2018, from the World Wide Web: http://trenmayamx.com/free-essays/It-Is-Amharic-603394.html